ሉቃስ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያ ሌሊቱን ሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስም ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጥቶ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነዚህም ወራት ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት ጌታችን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ። |
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
ዳንኤል ዐዋጁ ተፈርሞበት እንደ ጸና ቢያውቅም እንኳ ወደሚኖርበት ሰገነት ወጣ፤ የሚኖርበትም ሰገነት በኢየሩሳሌም ትይዩ የተከፈቱ መስኮቶች ነበሩት፤ ከዚህ በፊት ያደርገው እንደ ነበረም በጒልበቱ በመንበርከክ አምላኩን እያመሰገነ በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር።
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
ኢየሱስ ከሐዋርያቱ ጋር ከተራራው ወርዶ በሜዳ ላይ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ በዚያ ነበሩ፤ እንዲሁም ሊሰሙትና ከበሽታቸው ሊፈወሱ ፈልገው የመጡ፥ እጅግ ብዙ ሕዝብ ነበሩ። እነርሱም የመጡት ከይሁዳ ምድር ከኢየሩሳሌም ከተማ፥ በባሕር አጠገብ ከሚገኙት ከጢሮስና ከሲዶና ከተሞች ነበር።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።
“ሳኦል እኔን ትቶአል፤ ትእዛዜንም ስላልጠበቀ እርሱን በማንገሤ ተጸጸትሁ፤” ሳሙኤልም በዚህ ነገር ተቈጥቶ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ማለደ፤