ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ሉቃስ 5:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ አንድ ሽባ ሰው በአልጋ የተሸከሙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቤትም አግብተው በፊቱ ሊያኖሩት ፈልገው ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜም፣ ሰዎች አንድ ሽባ በቃሬዛ ተሸክመው አመጡ፤ ኢየሱስ ፊት ለማኖርም ወደ ቤት ሊያስገቡት ሞከሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ አንድ መንቀሳቀስ የማይችል ሰው በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አስገብተውትም በፊቱ ሊያኖሩት ይፈልጉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ሰዎች በአልጋ ተሸክመው ሽባ የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፤ እንዲፈውሰውም ወደ እርሱ ሊያስገቡት ወደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ አንድ ሽባ በአልጋ ተሸክመው አመጡ፤ አግብተውም በፊቱ ሊያኖሩት ይሹ ነበር። |
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለመደምሰስ ሥልጣን እንዳለው ማወቅ አለባችሁ” ብሎ ሽባውን ሰው፦ “አንተ ሰው ተነሥ፤ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ!” አለው።