ሉቃስ 22:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰዓት ያኽል ቈይቶም አንድ ሌላ ሰው ጴጥሮስን “ይህ ሰው ገሊላዊ ነውና በእርግጥ ከእርሱ ጋር ነበረ!” በማለት አጥብቆ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰዓት ያህል ቈይቶም፣ ሌላ ሰው በርግጠኛነት፣ “ይህ ሰው የገሊላ ሰው ስለ ሆነ በእውነት ከርሱ ጋራ ነበረ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰዓትም የሚያህል ቆይቶ ሌላ ሰው “እርሱ የገሊላ ሰው ነውና በእርግጥ ከእርሱ ጋር ነበረ!” ሲል አጥብቆ ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዲት ሰዓት ያህልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእውነት ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ሰውየውም የገሊላ ሰው ነው” ብሎ አስጨነቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰዓትም የሚያህል ቆይቶ ሌላው አስረግጦ፦ እርሱ የገሊላ ሰው ነውና በእውነት ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለ። |
እነርሱም “አብደሻል!” አሉአት። እርስዋ ግን “በእውነት እርሱ ነው!” ስትል አረጋገጠች፤ እነርሱም እንግዲያውስ “የእርሱ ጠባቂ መልአክ ይሆናል” አሉ።