እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
ሉቃስ 22:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚህ ነገር እውነተኛ ምሥጢር በእግዚአብሔር መንግሥት ፍጹም ሆኖ እስኪገለጥ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን የፋሲካ ራት ከቶ አልበላም እላችኋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት የዚህ ትርጕም እስኪፈጸም ድረስ ይህን ፋሲካ ዳግመኛ አልበላም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም እላችኋለሁና፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን፤ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ እንግዲህ ከእርሱ እንደማልበላ እነግራችኋለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው። |
እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
በማእድ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱ ኢየሱስ የተናገረውን ሰምቶ “በእግዚአብሔር መንግሥት በማእድ መቀመጥ የሚችል እንዴት የታደለ ነው!” አለ።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤
ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ በጉ ሠርግ ግብዣ የተጠሩ የተባረኩ ናቸው” ብለህ ጻፍ አለኝ፤ ቀጥሎም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው” አለ።