እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል።
ሉቃስ 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አካባቢ፥ በሜዳ ላይ ሌሊት መንጋቸውን እየጠበቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያው አገር በሌሊት መንጋቸውን ሲጠብቁ በሜዳ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም አካባቢ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ሀገር እረኞች ነበሩ፤ ሌሊቱንም ተግተው መንጋቸውን ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። |
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል።
በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።