“ነገር ግን ያ አገልጋይ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ሳለ መቶ ዲናር ያበደረውን የሥራ ጓደኛውን አገኘና አንገቱን አንቆ ይዞ፥ ‘ያበደርኩህን ገንዘብ ክፈለኝ!’ አለው።
ሉቃስ 16:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለተኛውንም ጠርቶ፥ ‘የአንተስ ዕዳ ምን ያኽል ነው?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ ዕዳ አለብኝ’ ሲል መለሰ። መጋቢውም ‘ይኸው የፈረምከው ውል! ሰማኒያ ዳውላ ብለህ ጻፍ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም ሌላውን፣ ‘አንተስ ስንት አለብህ?’ አለው። “እርሱም፣ ‘ዐምሳ ዳውላ ስንዴ’ አለው። “መጋቢውም፣ ‘የብድር ደብዳቤህን ዕንካ፤ “አርባ ዳውላ” ብለህ ጻፍ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኋላም ሌላውን ‘አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ፤’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛውንም፦ ‘አንተሳ ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ ሰማንያ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላም ሌላውን፦ አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ጫን ስንዴ አለ። ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ አለው። |
“ነገር ግን ያ አገልጋይ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ሳለ መቶ ዲናር ያበደረውን የሥራ ጓደኛውን አገኘና አንገቱን አንቆ ይዞ፥ ‘ያበደርኩህን ገንዘብ ክፈለኝ!’ አለው።
ጌታውም እምነት ያጐደለውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ ይህም ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ የዓለም ሰዎች በዓለማዊ ኑሮአቸው ብልኆች መሆናቸውን ያሳያል።
ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎች አከራየውና ወደ ሌላ አገር ሄደ፤ ሳይመለስም ብዙ ጊዜ ቈየ።