ንግሥተ ሳባ ስለ ሰሎሞን የሚነገረውን አስደናቂ ጥበብ ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ የእንቆቅልሽ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ስትመጣም ብዙ የክብር አጃቢዎችን አስከትላ ሽቶ፥ የከበሩ ዕንቆችና እጅግ የበዛ ወርቅ በግመሎች አስጭና ነበር፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኘች ጊዜ በሐሳብዋ የነበረውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤
ሉቃስ 11:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደቡብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ በእርሱ ላይ ትፈርዳለች፤ እርስዋ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከዓለም ዳርቻ መጥታለች፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደቡቧ ንግሥት በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ እርሷ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፤ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግሥተ አዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ትነሳለች፥ በእነርሱም ላይ ትፈርዳለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዜብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፋረዳቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ልትሰማ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ። |
ንግሥተ ሳባ ስለ ሰሎሞን የሚነገረውን አስደናቂ ጥበብ ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ የእንቆቅልሽ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ስትመጣም ብዙ የክብር አጃቢዎችን አስከትላ ሽቶ፥ የከበሩ ዕንቆችና እጅግ የበዛ ወርቅ በግመሎች አስጭና ነበር፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኘች ጊዜ በሐሳብዋ የነበረውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
የደቡብ ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለ መጣች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥታ በእርሱ ላይ ትፈርድበታለች፤ አሁን ግን ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።”
መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ወረደ፤ በዚያኑ ጊዜ “አንተ የተወደድክ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።