በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
ሉቃስ 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከእርሱ የበለጠ ኀይለኛ ሰው መጥቶ ካሸነፈው የተማመነበትን የጦር መሣሪያ ይወስድበታል ንብረቱንም ሁሉ ዘርፎ ያካፍላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ አደጋ ጥሎበት ካሸነፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን የጦር ዕውቃን ይወስድበታል፤ ምርኮውንም ያካፍላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ የሚበረታው ቢመጣና ቢያሸንፈው ግን፥ ይታመንበት የነበረውን የጦር መሣሪያውን ይገፈዋል፤ የማረከውንና የዘረፈውን ገንዘቡንም ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ ወጥቶ ሲያሸንፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን ጋሻና ጦር ይወስድበታል ምርኮውንም ያካፍላል። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።
ሕይወቱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፤ ከክፉ አድራጊዎችም ጋር ተቈጠረ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የብዙዎችን ኃጢአት ተሸከመ፤ ለበደለኞችም ማለደ፤ ስለዚህ እኔ ከታላላቆቹ ጋር ድርሻ እንዲኖረውና ከኀያላን ጋር ምርኮን እንዲካፈል አደርገዋለሁ።”
ስለዚህ በክፉ ቀን የጠላትን ኀይል ለመቋቋም እንድትችሉና ሁሉንም ፈጽማችሁ ጸንታችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር መሣሪያ አንሡ!
ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንሥቶ ኃጢአት ስለሚሠራ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የዲያብሎስ ወገን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።
ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።