ሉቃስ 11:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ኢየሱስ የማያናግር ጋኔን ከአንድ ድዳ ሰው ያስወጣ ነበር፤ ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ድዳው ሰው መናገር ጀመረ፤ ሕዝቡም በዚህ ነገር እጅግ ተደነቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ኢየሱስ ድዳ ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣለት በኋላ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም ተገረመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መናገርም የተሳነውን ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ መናገር የተሳነው ሰው ተናገረ፥ ሕዝቡም ተደነቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲዳና ደንቆሮ ጋኔንንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደንቆሮ የነበረው ተናገረ፤ ሰዎችም አደነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲዳውንም ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ ሕዝቡም ተደነቁ፤ |
ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ተደነቀ፤ ይከተሉት የነበሩትን ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ይህን የሚያኽል ትልቅ እምነት ያለው አንድም ሰው በእስራኤል ስንኳ አላገኘሁም።