ሰቈቃወ 3:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃ ከእራሴ በላይ ሞልቶ ሲፈስ የምሞትበት ጊዜ የተቃረበ መሰለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፥ እኔም፦ ጠፋሁ ብዬ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራሴ ላይ ውኃ ተከነበለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፥ እኔም፦ ጠፋሁ ብዬ ነበር። |
በእርሱ ላይ የተዛባ ፍርድ ተወስኖበት ተወሰደ፤ የወደፊትስ ሁኔታውን ማስተዋል የሚችል ማነው? ሆኖም ስለ ሕዝቤ መተላለፍ ተመታ፤ ከሕያዋንም ዓለም ተወገደ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ እኮ ልክ እንደእነዚህ አጥንቶች ናቸው፤ እነርሱ ‘እነሆ፥ አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ ቈርጠናል፤ የእኛ ጉዳይ አልቆለታል’ ይላሉ።