ኢያሱ 9:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያሱ፥ ከእስራኤል ሕዝብ ወገን ማንም እንዳይገድላቸውና ተጠብቀው እንዲኖሩ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤላውያን እጅ አዳናቸው፤ እነርሱም አልገደሏቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አደረገባቸው፥ ከእስራኤልም ልጆች እጅ አዳናቸው፥ አልገደሉአቸውምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም እንዲሁ አደረገባቸው፤ ከእስራኤልም ልጆች እጅ አዳናቸው፤ አልገደሉአቸውምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም አደረገባቸው፥ ከእስራኤልም ልጆች እጅ አዳናቸው፥ አልገደሉአቸውምም። |
ነገር ግን በዚሁ ጊዜ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለእስራኤል ሕዝብና ለእግዚአብሔር መሠዊያ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። እነርሱም እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ቦታ፥ ይህንኑ አገልግሎት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።