ኢያሱ 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን በማድረጋችሁ ምክንያት እግዚአብሔር ፈርዶባችኋል፤ ስለዚህም የእናንተ ሕዝብ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለዘለዓለም አገልጋዩ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ ጥቂቶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ምን ጊዜም ዕንጨት ቈራጭ፣ ውሃ ቀጂ ባሮች ትሆናላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሁን የተረገማችሁ ናችሁ፤ እናንተም ለአምላኬ ቤት እንጨት ቈራጭ ውኃም ቀጂ ባርያዎች ለዘለዓለም ትሆናላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም የተረገማችሁ ሁኑ፤ ለእኔም፥ ለአምላኬም እንጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእናንተ አይጠፋም” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም የተረገማችሁ ናችሁ፥ ለአምላኬም ቤት እንጨት ቈራጭ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእናንተ ለዘላለም አይጠፋም አላቸው። |
ነገር ግን በዚሁ ጊዜ እንጨት በመቊረጥና ውሃ በመቅዳት ለእስራኤል ሕዝብና ለእግዚአብሔር መሠዊያ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። እነርሱም እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ቦታ፥ ይህንኑ አገልግሎት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።