ኢያሱ 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምምነቱ በተደረገ በሦስተኛውም ቀን እነዚህ ሰዎች ጐረቤቶቻቸው መሆናቸውንና በመካከላቸውም እንደሚኖሩ ሰሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከገባዖን ሰዎች ጋራ ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ ጎረቤቶቻቸው እንደ ሆኑ በመካከላቸውም እንደሚኖሩ ሰሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ ከቅርብ እንደሆኑና በአጠገባቸው እንደሚኖሩ ሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ ጎረቤቶቻቸው እንደ ሆኑ በመካከላቸውም እንደ ኖሩ ሰሙ። |
ስለዚህም ኢያሱ ከእነርሱ ጋር ለሕይወታቸው ዋስትና ቃል ኪዳን በመግባት የሰላም ስምምነት አደረገ። የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችም ስምምነቱን ለመጠበቅ ቃል ገቡላቸው።
ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጒዞ ጀምረው ከሦስት ቀን በኋላ እነዚህ ሕዝብ ወደሚኖሩባቸው ከተሞች ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ በኤሮትና ቂርያትይዓሪም ተብለው ይጠሩ ነበር፤
ኢያሱም የገባዖንን ሕዝብ ወደ እርሱ ፊት እንዲቀርቡ አድርጎ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ “በዚሁ በቅርብ የምትኖሩ ሲሆን፥ በጣም ሩቅ ከሆነ አገር የመጣን ነን ብላችሁ ስለምን አታለላችሁን?