የገቡትን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ መሆናቸውንም በማረጋገጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በእግዚአብሔር ስም ማሉ፤ ከዚህም በኋላ በጥሩምባና በእምቢልታ ድምፅ ታጅበው በሆታና በእልልታ ደስታቸውን ገለጡ።
ኢያሱ 24:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ኢያሱን “እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ትእዛዞችንም እንፈጽማለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ኢያሱን፣ “እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ እንታዘዝለታለንም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ኢያሱን፦ “ጌታ አምላካችንን እናገለግላለን፥ ድምፁንም እንሰማለን” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ኢያሱን፥ “አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ ቃሉንም እንሰማለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን አሉት። |
የገቡትን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ መሆናቸውንም በማረጋገጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በእግዚአብሔር ስም ማሉ፤ ከዚህም በኋላ በጥሩምባና በእምቢልታ ድምፅ ታጅበው በሆታና በእልልታ ደስታቸውን ገለጡ።
ሙሴም ሄዶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ለሕዝቡ ነገረ፤ ሕዝቡም በአንድነት “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” ሲል መለሰ።
ከዚህ በኋላ የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ፤ ሕዝቡም “ለእግዚአብሔር እንታዘዛለን እርሱ ያዘዘውንም ሁሉ እንፈጽማለን” አሉ።
መልካም ቢሆንም ባይሆንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቃል እንታዘዛለን፤ ወደ እርሱ የምንልክህም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብናከብር ሁሉ ነገር የሚሳካልን በመሆኑ ነው።”