ዮሐንስ 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በእርሱ ወይም በወላጆቹ ኃጢአት ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም፤ ይህ የሆነው ግን የእግዚአብሔር ሥራ በርሱ ሕይወት እንዲገለጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔር ሥራ ሊገለጥበት ነው እንጂ እርሱ አልበደለም፤ ወላጆቹም አልበደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም እንዲ ብሎ መልሰ፦ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም። |
እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ።
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ።
የሕዝብ አለቆችና የሸንጎው አባሎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን የሚያስቀጣ ምንም ምክንያት ባለማግኘታቸው፥ ሕዝቡንም ስለ ፈሩ እንደገና አስጠንቅቀው ለቀቁአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግን ስለ ነበር ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።