ዮሐንስ 7:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያሉበት ምክንያት ወንድሞቹ እንኳ በእርሱ ስላላመኑ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገዛ ወንድሞቹ እንኳ አላመኑበትም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹም እንኳን አላመኑበትም ነበርና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹ ገና አላመኑበትም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹ ስንኳ አላመኑበትም ነበርና። |
ስለዚህ ወንድሞቹ ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “ደቀ መዛሙርትህ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ፤
በግልጥ ለመታወቅ የሚፈልግ ሰው ሥራውን በስውር አያደርግም፤ አንተም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስታደርግ ራስህን ለዓለም ልትገልጥ ያስፈልጋል።”