አገልጋዮቹን፥ “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሞት ተነሥቶአል፤ እነዚህ ድንቅ ነገሮች በእርሱ አማካይነት የሚደረጉት ስለዚህ ነው” አላቸው።
ዮሐንስ 10:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው “ዮሐንስ ምንም ተአምር አላደረገም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጡ። እነርሱም፣ “ዮሐንስ አንድም ታምራዊ ምልክት አላደረገም፤ ነገር ግን ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው “ዮሐንስ አንድ ምልክት እንኳን አላደረገም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ፤” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎችም ወደ እርሱ ሄደው፥ “ዮሐንስ ምንም ያደረገው ተአምራት የለም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ሆነ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው፦ “ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ” አሉ። |
አገልጋዮቹን፥ “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሞት ተነሥቶአል፤ እነዚህ ድንቅ ነገሮች በእርሱ አማካይነት የሚደረጉት ስለዚህ ነው” አላቸው።
በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከብዛታቸውም የተነሣ እርስ በርሳቸው እየተጋፉ ይረጋገጡ ነበር፤ ኢየሱስም በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ማለትም ከግብዝነታቸው ተጠንቀቁ ማለት ነው።
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።