ዮሐንስ 1:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ “እኔ መሲሕ አይደለሁም” ሲል መሰከረ እንጂ አልካደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመመስከርም ወደ ኋላ አላለም፤ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤” ብሎ በግልጽ መሰከረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሰከረም፤ አልካደምም፤ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤” ብሎ መሰከረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ አመነ እንጂ አልካደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሰከረም አልካደምም እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ። |
ዮሐንስ ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ‘እኔ ማን መሰልኳችሁ? እኔ መሲሕ አይደለሁም፤ ነገር ግን የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ከእኔ በኋላ ሌላ ይመጣል’ ይል ነበር።