ኢዮብ 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእርግጥ እናንተ በጣም ብልኆች ናችሁ፤ ስትሞቱም ጥበብ ከእናንተ ጋር የምትሞት ይመስላችኋል! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናችኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋራ ትሞታለቻ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእርግጥም እናንተ የሕዝብ ድምፅ ናችኋ! ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእርግጥ እናንተ ዓይነተኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበብም በእናንተ ዘንድ ትፈጸማለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርግጥ እናንተ ዓይነተኞች ሰዎች ናቸሁ፥ ጥበብም ከእናንተ ጋር ይሞታል። |
እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል።