እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን?
ኢዮብ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰይጣንም እንዲህ አለ፦ “ኢዮብ አንተን እግዚአብሔርን የሚፈራ ያለ ምክንያት ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይጣንም፣ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይጣንም ለጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይጣንም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብሎ መለሰ፥ “በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚያመልከው በከንቱ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይጣንም ለእግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን? |
እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን?
“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳትን ከምታቃጥሉበት ይልቅ የቤተ መቅደሱን በር የሚዘጋ ምነው ከእናንተ አንድ ሰው እንኳ በተገኘ! በእናንተ ደስ ስለማይለኝ ለእኔ የምታቀርቡትን ቊርባን አልቀበልም፤
በሰውነት ማጠንከሪያ ትምህርት ራስን ማለማመድ ጥቅሙ ጥቂት ነው፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለማመድ ግን ለአሁንና ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።
“ያለኝ ይበቃኛል” ለሚል ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል። መንፈሳዊነትን ስለሚያተርፍበት ሃይማኖት የሀብት ምንጭ ነው።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።