ሰውየውም የመግቢያውን መተላለፊያ ሲመትር ስምንት ክንድ ሆኖ አገኘው፤ የግንቦቹ ስፋት ሁለት ክንድ ሆነ፤ የበሩ መተላለፊያ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያመራ ነበር።
ኤርምያስ 31:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወሰኑም መስመር ከማእዘኑ ቅጥር በር ወደ ጋሬብ ኰረብታ ይሄድና ወደ ጎዓ ይዞራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መለኪያ ገመዱም ከዚያ ጀምሮ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኰረብታ፣ ዐልፎም ወደ ጎዓ ይዘረጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመለኪያውም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፥ ከዚያም ወደ ጎዓም ይዞራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጠንዋ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጎዓትም ይዞራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፥ ወደ ጎዓም ይዞራል። |
ሰውየውም የመግቢያውን መተላለፊያ ሲመትር ስምንት ክንድ ሆኖ አገኘው፤ የግንቦቹ ስፋት ሁለት ክንድ ሆነ፤ የበሩ መተላለፊያ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያመራ ነበር።