ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
ኤርምያስ 23:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ መካከል በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ቆሞ ቃሉን ያዳመጠና ለቃሉም ትኲረት ሰጥቶ ታዛዥ የሆነ ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃሉን ለማየትና ለመስማት፣ እነማን የእግዚአብሔር ምክር ባለበት ቆመዋል? ቃሉን ያደመጠ፣ የሰማስ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሉን ለማየትና ለመስማት በጌታ ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ምክር የሚቆም፥ ቃሉን የሚያይና የሚሰማ ማን ነው? ቃሉንስ ያዳመጠ፥ የሰማስ ማንነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው? |
ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ መታውና “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
በእኔ ጉባኤ ፊት ቆመው ቢሆንማ ኖሮ ቃሌን ለሕዝቡ ባወጁ ነበር፤ ጠማማ መንገዳቸውንና ክፉ አኗኗራቸውንም ትተው ወደ እኔ እንዲመለሱ ማድረግ በቻሉ ነበር።”
አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤
ይህም፦ “የጌታን ሐሳብ ማን ሊያውቀው ይችላል? ሊመክረውስ የሚችል ማን ነው?” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።