ያዕቆብ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቁንስ እናንተ ማለት የሚገባችሁ “ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁንም፣ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም፥ “የጌታ ፈቃድ ቢሆን እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ፈንታ “ጌታ ቢፈቅድ፥ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፤” ማለት ይገባችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ፈንታ፦ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። |
ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ የእነዚህን ትዕቢተኞች ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን ኀይላቸውንም ማወቅ እፈልጋለሁ።