ኢሳይያስ 42:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እግዚአብሔርን ያክብሩ፤ በጠረፍ አገሮችም ላይ ምስጋናውን ያውጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብር ለእግዚአብሔር ይስጡ፤ ምስጋናውንም በደሴቶች ያውጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ክብርን ይስጡ፥ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፤ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፥ ምሥጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ። |
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”
አገራችሁን ለማጥፋት በተላኩት አይጦችና እባጮች አምሳል እነዚህን ስጦታዎች ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር መስጠት አለባችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ምናልባት እናንተን፥ አማልክታችሁንና ምድራችሁን የሚቀጣበትን መቅሠፍት ያነሣ ይሆናል፤