ኢሳይያስ 41:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፦ እንዲህ ይላል፦ “ጉዳያችሁን አቅርቡ፤ ማስረጃችሁንም አምጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ማስረጃችሁን አምጡ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙግታችሁን ይዛችሁ ቅረቡ፥ ይላል ጌታ፤ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዳችሁ ቀረበች፥ ይላል እግዚአብሔር አምላክ፤ ምክራችሁም ቀረበ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክርክራችሁን አቅርቡ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ማስረጃችሁን አምጡ፥ ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በደሴቶች የምትኖሩ ሕዝቦች! ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! ሕዝቦች ኀይላቸውን ያድሱ፤ ወደ ፊትም ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድ ሸንጎ በአንድነት እንገናኝ።
ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፤ ከእነርሱ መካከል የአሁንና የቀድሞዎቹን ነገሮች አስቀድሞ የተናገረና የገለጠ ማነው? እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያምጡ። እነርሱም ሰምተው እውነት ነው ይበሉ።
የሠራዊት አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥና አዳኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም።
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።