በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
ኢሳይያስ 40:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው? ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍትህንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? ፍርድንስ ማን አስተማረው? የጥበብንስ መንገድ ማን አሳየው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው? |
በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም።
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።