በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤ የወይን ተክልም አብቦአል፤ የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤ ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ።
ኢሳይያስ 18:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣ አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣ የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ፥ አበባው ያበበ የወይንም ፍሬ ሲይዝ፥ የወይኑን ዘንግ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ ጫፎቹንም መልምሎ ያስወግዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፤ ጫፎቹንም ይመለምላል፤ ያስወግድማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፥ ጫፎቹንም ይመለምላል ያስወግድማል። |
በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤ የወይን ተክልም አብቦአል፤ የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤ ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤ የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ።
እነሆ የሠራዊት አምላክ ከዛፍ እንደ ተቈረጠ ቅርንጫፍ እየሰባበረ ያወርዳቸዋል፤ በእነርሱ መካከል ኩራተኛ የሆነውና እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ የታበየው ይዋረዳል።
የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።