እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።
ዕብራውያን 8:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ነቀፋ የሌለው ሆኖ ቢገኝ ኖሮ ሁለተኛው ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጕድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊተኛው ኪዳን ጉድለት ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊተኛይቱ ያለ ነቀፋ ብትሆን ኖሮ ሁለተኛይቱን ባልፈለገም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። |
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።
እንግዲህ ለሕዝቡ ሕግ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ነው፤ በዚህ በሌዋውያን ክህነት ፍጹምነት ቢገኝ ኖሮ የአሮን የክህነት ሹመት ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣት ባላስፈለገም ነበር፤
አሁን ግን ኢየሱስ አማካይ አስማሚ የሆነበት ቃል ኪዳን ከአሮጌው ቃል ኪዳን የበለጠና በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ እንደ መሆኑ ለእርሱ የተሰጠው አገልግሎት የበለጠ ነው።