ዕብራውያን 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእነዚያ ቀኖች በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም እጽፈዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከነዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ “በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ፥ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእነዚያ ወራቶች በኋላ የምገባላቸው ኪዳን ይህቺ ናት ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልባቸው አኖረዋለሁ፤ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ካለ በኋላ። |