ዘፍጥረት 9:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ ስካሩ አልፎለት ሲነቃ፥ ትንሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፥ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም ከወይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም ከወይን ጠጅ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። |
ሴምና ያፌትም ልብስ በስተኋላቸው፥ በትከሻቸው ያዙ፤ ወደ ድንኳኑም የኋሊት ሄዱና የአባታቸውን ራቊትነት እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው ራቊትነቱን ሸፈኑ፤ የአባታቸውንም ራቊትነት ኣላዩም።