ዘፍጥረት 9:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ካም የከነዓን አባት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። |
እግዚአብሔርም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “ይህ ቀስት በምድር ላይ በእኔና ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች ሁሉ መካከል የገባሁትን ቃል ኪዳን የሚያስታውስ ምልክት ነው።”
ሴምና ያፌትም ልብስ በስተኋላቸው፥ በትከሻቸው ያዙ፤ ወደ ድንኳኑም የኋሊት ሄዱና የአባታቸውን ራቊትነት እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው ራቊትነቱን ሸፈኑ፤ የአባታቸውንም ራቊትነት ኣላዩም።