ዘፍጥረት 6:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲጠበቁ ሥጋ ከለበሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ከየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየወሰድህ ወደ መርከቡ አስገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንተ ጋራ በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለት እያደረግህ ወደ መርከብ ታስገባለህ፥ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንስሳ ሁሉ፥ ከተንቀሳቃሽ አራዊትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአንተ ጋር ትመግባቸው ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለር እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ ተባትና እንስት ይሁን። |
ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።”
እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።