ዘፍጥረት 41:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች ምድሪቱ እጅግ ብዙ ሰብል ሰጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ግብፅ ያስገኘችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። |
ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤
በግብጽ አገር በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመቶች የተገኘውን ሰብል ሰብስቦ በየከተሞች አከማቸ፤ በየእያንዳንዱ ከተማ ያከማቸው እህል በዙሪያው ከሚገኙት እርሻዎች የተመረተ ነበር።
በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤ ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤ የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።