ዘፍጥረት 41:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተከታዩ የራብ ዘመን እጅግ አሠቃቂ ስለሚሆን የጥጋብ ጊዜ ፈጽሞ እንዳልነበረ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፥ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላም ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣ በምድር የሆነው ጥጋብ አይታወቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኍላ ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣም በምድር የሆነው ጥጋብ አያታወቅም እጅግ ጽኑ ይሆናልና። |
ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።