ዘፍጥረት 41:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመላው የግብጽ ምድር ላይ ታላቅ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመቶች ይመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመላው የግብጽ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመላው የግብጽ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ |
በዚህ ዐይነት ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነ እጅግ ብዙ እህል አከማቸ፤ እህሉ እጅግ ብዙ ከመሆኑ የተነሣ እየሰፈረ መጠኑን ለማወቅ የነበረውን ዕቅድ ተወ።