ዘፍጥረት 41:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀጨጩትም ዛላዎች የሚያምሩትን ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርኩ፤ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጒምልኝ አልቻለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ የሰለቱትና በነፋስ የተመቱት እሸቶች እነዚያን ያማሩትንና የጐመሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ፤ የተረጐመልኝም የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ። |
ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።
አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።
“በመንተባተብ የሚቀባጥሩትን ሟርተኞችንና የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ” እያሉ የሚሰብኩአችሁ ወገኖች አሉ፤ ታዲያ፥ ስለ ሕያዋን ሙታንን ከመጠየቅ ይልቅ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን?
ጠንቋዮች፥ አስማተኞች፥ ኮከብ ቈጣሪዎችና መተተኞች ሁሉ ወደ እኔ በመጡ ጊዜ ሕልሜን ነገርኳቸው፤ እነርሱ ግን የሕልሜን ትርጒም ሊነግሩኝ አልቻሉም፤