ዘፍጥረት 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ቀን በኋላም ቃየል ካመረተው ሰብል ወስዶ ለእግዚአብሔር መባ አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ ወቅት፣ ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለጌታ መሥዋዕትን አቀረበ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ቀን በኋላም እንዲህ ሆነ፤ ቃየል ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብዙ ቀን በኍላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። |
አቤልም ከበጎቹ መንጋ በመጀመሪያ የተወለደውን አንድ ጠቦት አመጣ፤ ካረደውም በኋላ የሰባውንና መልካም የሆነውን ብልት ሁሉ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ አለው።
ይህም ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርኩም፤ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሠላሳ ሁለተኛው ዓመት ወደ ባቢሎን ተመልሼ ሄጄ ነበር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከንጉሡ ፈቃድ ጠይቄ፥