መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው፤ መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት በሚመጡበት ጊዜ፥
ዘፍጥረት 30:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ፣ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎቹ ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፥ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፦ በጎቹ በሚፀንሱበት ወራት በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በበጎቹ ፊት በውኃ ማጠጫ ገንዳው ውስጥ ያኖራቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፤ |
መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው፤ መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት በሚመጡበት ጊዜ፥
ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጒርጒርና ጥቊር በሆኑት በላባ መንጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዐይነት የራሱን መንጋ ወደ ላባ መንጋ ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው።
ነገር ግን በትሮቹን በደካሞቹ መንጋዎች ፊት ለፊት አያስቀምጣቸውም ነበር፤ በዚህ ዐይነት ደካሞቹ መንጋዎች ለላባ ሲሆኑ ብርቱዎቹ ግን የያዕቆብ ሆኑ።