ዘፍጥረት 30:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጒርጒርና ጥቊር በሆኑት በላባ መንጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዐይነት የራሱን መንጋ ወደ ላባ መንጋ ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ግልገሎቹን ለብቻ ለያቸው፤ የቀሩትንም የላባ መንጎች ሽመልመሌና ጥቋቍር በሆኑት በጎች ትይዩ አቆማቸው፤ በዚህም መሠረት የራሱ መንጋ ከላባ መንጋ ጋራ እንዳይቀላቀል ለብቻ ለየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፥ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ተባት በጎችንና እንስት በጎችን ለይቶ ነጭና ሐመደ ክቦ በሆኑ አውራዎች ፊት አቆማቸው፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው። ከላባ በጎች ጋርም አልጨመራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም። |
ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር።