በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔል ልያን “እባክሽ ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
ዘፍጥረት 30:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ምሽት ያዕቆብ ከዕርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለ ተከራየሁህ የዛሬው ዐዳርህ ከእኔ ጋራ ነው” አለችው፤ ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከርሷ ጋራ ዐደረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ “ወደ እኔ ትገባለህ፥ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና።” በዚያችም ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልትቀበለው ወጣች፤ እንዲህም አለችው፥ “እኔ ዘንድ ታድራለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተስማምቼሃለሁና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ ወደ እኔ ትገባለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና። በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር ተኛ። |
በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔል ልያን “እባክሽ ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
ልያም “ባሌን የነጠቅሽኝ አንሶሽ፥ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣልኝን እንኮይ መቀማት ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “ከልጅሽ እንኮይ ስጪኝና ዛሬ ሌሊት ያዕቆብ ካንቺ ጋር ይደር” አለቻት።