እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
ዘፍጥረት 21:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ ሐሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይሥሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው “ስለ ባርያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፥ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፥ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ስለዚች አገልጋይህና ስለ ሕፃኑ አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
ነገር ግን ቅዱስ መጽሐፍ የሚለው ምንድን ነው? ቅዱስ መጽሐፍ “አገልጋይቱ ሴት የወለደችው ልጅ ነጻይቱ ሴት ከወለደችው ልጅ ጋር አብሮ ስለማይወርስ አገልጋይቱን ከነልጅዋ ወዲያ አስወጣት” ይላል።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ የሚሉህን ነገር ሁሉ ተቀበል፤ እነርሱ የናቁት አንተን አይደለም፤ በእነርሱ ላይ ነግሼ እንዳልኖር፥ እነርሱ የናቁት እኔን ነው።
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ የሚሉህን ተቀበል፤ ነገር ግን ንጉሦቻቸው ወደ ፊት በእነርሱ ላይ የሚፈጽሙባቸውን ነገር ሁሉ በመግለጥ በብርቱ አስጠንቅቃቸው።”