ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ዘፍጥረት 2:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአትክልት ቦታውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር፤ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፥ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለዐራት መዓዝን ይከፈል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ከአራት ክፍል ይከፈል ነበር። |
ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።