La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብራም በከነዓን ኖረ፤ ሎጥ ግን በሸለቆው ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል ተቀመጠ፤ በሰዶምም አጠገብ ድንኳኑን ተከለ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል በሰዶም አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜዳ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ሰዶምም ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 13:12
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሎጥ መላውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ለራሱ መረጠና ወደ ምሥራቅ ሄደ፤ ሁለቱ የተለያዩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤


የአብራም የወንድም ልጅ ሎጥ በሰዶም ይኖር ስለ ነበር እርሱን ማርከው፥ ሀብቱንም ሁሉ ይዘው ሄዱ።


እነዚህ አራቱ ነገሥታት፥ ሌሎችን አምስት ነገሥታት ለመውጋት ሄዱ፤ የተዘመተባቸውም አምስት ነገሥታት የሰዶም ንጉሥ ቤራዕ፥ የገሞራ ንጉሥ ቢርሻዕ፥ የአዳማ ንጉሥ ሺንአብ፥ የጸቦይም ንጉሥ ሼሜቤርና ጾዓር ተብላ የምትጠራው የቤላዕ ንጉሥ ነበሩ።


በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥


እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ከተሞች ላይ እሳትና ዲን ከራሱ (ከእግዚአብሔር ዘንድ) ከሰማይ አዘነበ።


በዚህ ዐይነት እነዚያን ከተሞችና ሸለቆዎች፥ እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፥ በምድሩም ላይ የበቀለውን ነገር ሁሉ ደመሰሰ።


ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።


የክፉ አድራጊዎችን ጉባኤ እጠላለሁ፤ ከክፉዎችም ጋር መቀመጥ አልፈቅድም።


አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”