እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
ዘፍጥረት 10:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ የሴም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባችው እነዚህ ናቸው። |
እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።
እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።