ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ ለእነዚህ ምሰሶዎች ከነሐስ የተሠሩ አምስት እግሮች አብጅላቸው።
ዘፀአት 38:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ የሆነው ደጃፍ የሚቆምባቸውን እግሮች፥ ከነሐስ መከላከያው ጋር የነሐስ መሠዊያውን፥ ለመሠዊያው መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ከዚህ ነሐስ ሠራ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ለናስ መሠዊያው ከናስ መጫሪያው፣ ለዕቃዎቹም ሁሉ መቆሚያዎቹን ለመሥራት አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ እግሮች፥ የነሐሱን መሠዊያ፥ ለእርሱም የሚያገለግለውን የነሐሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ ሠራ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም የምስክሩን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም የመገናኛውን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ |
ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ ለእነዚህ ምሰሶዎች ከነሐስ የተሠሩ አምስት እግሮች አብጅላቸው።
በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን።
በዙሪያ ያለው የአደባባይ አጥርና ወደ አደባባዩ የሚያስገባው ደጃፍ የሚቆሙባቸውን እግሮች፥ እንዲሁም የድንኳኑና በዙሪያው ያለውን የአደባባይ አጥር ካስማዎችን ሁሉ ሠራ።