ዘፀአት 27:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሠዊያው መሸከሚያ የሚሆኑ መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በነሐስ ለብጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የግራር ዕንጨት መሎጊያዎችን ለመሠዊያው ሠርተህ በንሓስ ለብጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመሠዊያው ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በነሐስም ለብጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመሠዊያውም ከማይነቅዝ ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርተህ በናስ ለብጣቸው፤ መሎጊያዎቹም በቀለበቶች ውስጥ ይግቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመሠዊያውም ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሠርተህ በናስ ለብጣቸው። |