ኤፌሶን 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕፍረት ስሜታቸው ስለ ጠፋ ርኲሰቶችን ሁሉ ለመፈጸም ራሳቸውን ለሥጋዊ ምኞታቸው አሳልፈው ሰጥተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ፥ በማይረካ ምኞት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ለሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተስፋ የቈረጡ ናቸው፤ ራሳቸውንም ለጕስቍልና፥ ለርኵሰትና ለመዳራት አሳልፈው ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ። |
እነርሱ በልተው እንደማይጠግቡ ውሾች ናቸው። የማያስተውሉም እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ፤ እያንዳንዱም የራሱን ጥቅም ያሳድዳል።
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
እንዲህም ዐይነቱ ትምህርት የሚመነጨው በግብዝነት፥ ሐሰትን ሲናገሩ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ያኽል ሆኖ የደነዘዘ ኅሊናቸው ከማይወቅሳቸው ሰዎች ነው።
አሕዛብ እንደሚያደርጉት በስድነት፥ በፍትወት፥ በስካር፥ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያ፥ ያለ ልክ ጠጥቶ በመጨፈርና አጸያፊ በሆነ የጣዖት አምልኮ ያሳለፋችሁት ዘመን ይበቃል።
“የተፋውን ለመዋጥ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል።” እንዲሁም “ዐሣማ ከታጠበ በኋላ ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል።
የሚያሰክረውን የአመንዝራነትዋን ወይን ጠጅ ለሕዝቦች ሁሉ አጠጥታለች፤ የምድር ነገሥታት ከእርስዋ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ነጋዴዎችም ከብዙ ምቾትዋ የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋል።”