La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤፌሶን 3:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም የሚያመለክተው አሕዛብ ከአይሁድ ጋር የርስቱ ወራሾችና የአንድ አካል ክፍሎች ሆነው እግዚአብሔር ለሰጠው ተስፋ በወንጌል አማካይነት በኢየሱስ ክርስቶስ ተካፋዮች መሆናቸውን ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት ከእስራኤል ጋራ ዐብረው ወራሾች፣ ዐብረው የአንዱ አካል ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ ዐብረው ተካፋይ መሆናቸው ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሕ​ዛ​ብን ወራ​ሾ​ቹና አካሉ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ፥ በወ​ን​ጌ​ልም ትም​ህ​ርት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።

Ver Capítulo



ኤፌሶን 3:6
17 Referencias Cruzadas  

ዘላቂ ርስትም ትሁንላችሁ፤ ልጆች ወልደው በመካከላችሁ የሚኖሩ ባዕዳንም ምድሪቱን በምትካፈሉበት ጊዜ የራሳቸው ድርሻ ይኑራቸው፤ እንደማንኛውም እስራኤላውያን ዜጋ ተቈጥረው ምድሪቱን ከሚካፈሉት ከእስራኤል ነገዶች ጋር ዕጣ እንዲጣልላቸው ያስፈልጋል።


አንድ ሰው ብዙ የአካል ክፍሎች አሉት፤ የአካል ክፍሎች ብዙዎች ሆነው ሳሉ የሚገኙት በዚያው በአንዱ አካል ነው። እንዲሁም ክርስቶስ ብዙ የሰውነት ክፍሎች እንዳሉት እንደ አንድ አካል ነው።


እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ክፍሎች ናችሁ።


ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።


የኢየሱስ ክርስቶስ የሆኑት ሰዎች ሥጋን ከፍትወቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል።


አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍኩላችሁ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ገልጦ በራእይ አሳይቶኛል።


እኛም የክርስቶስ አካል ክፍሎች ነን፤


ስለዚህ ከእነዚህ ከማይታዘዙ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤


እንዲህ ያለ ሰው ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ አካልን በሙሉ በመገጣጠሚያና በጅማት አያይዞ የሚመግበው ራስ ነው። እግዚአብሔር ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠውም በዚህ ዐይነት ነው።


ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን። አንድነታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።


ይህም ክርስቶስ የሰጠን ተስፋ የዘለዓለም ሕይወት ነው።