መክብብ 7:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ “እነሆ፦ በተከታታይ መርምሬ ያገኘሁት ሌላ ነገር ደግሞ ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባኪው እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው፤ “የነገሮችን ብልኀት መርምሮ ለማግኘት፣ አንዱን በአንዱ ላይ በመጨመር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱን በአንዱ ላይ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ ትርጒም እደርስ ዘንድ፥ እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ መደምደሚያን ለማግኘት አንዲቱን በአንዲቱ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደምደሚያ እደርስ ዘንድ ብመረምር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱን በአንዱ ላይ ጨምሬ ወደ ነገሩ ሁሉ መደምደሚያ እደርስ ዘንድ፥ እነሆ፥ ይህን ነገር አገኘሁ ይላል ሰባኪው፥ |
ከሞት ይልቅ የመረረ ሌላም ነገር አገኘሁ፤ ይኸውም የሴት ወጥመድነት ነው፤ ሴት እንደ መረብ በሆነ ፍቅርዋ ወንዶችን ታጠምዳለች፤ እንደ እግር ብረት በሆኑ ክንዶችዋም ተጠምጥማ ለመያዝ ትፈልጋለች፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ብቻ ከእርስዋ ሸሽቶ ማምለጥ ይችላል፤ ኃጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ይኸውም ሌላ መልስ ለማግኘት ፈልጌ ማጣቴ ነው፤ ከሺህ ወንዶች መካከል ልበ ቅን ሊባል የሚገባ አንድ ወንድ ብቻ አገኘሁ፤ ከሴቶች መካከል ግን አንዲት እንኳ ማግኘት አልቻልኩም።