ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን?
ዘዳግም 24:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ወጥታችሁ በጒዞ ላይ ሳላችሁ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ አምላክህ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ ጌታ እግዚአብሔር በማርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ከግብፅ ባወጣችሁ ጊዜ በመንገድ ሳላችሁ በማርያም ላይ ያደረገውን ዐስብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ በመንገድ ሳላችሁ በማርያም ላይ ያደረገውን አስብ። |
ሰውነታቸው የቆዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች ከሰማርያ ቅጽር በር ውጪ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ ስለምን በዚህ እንቈያለን?
“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤
ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው።